ለውጭ ሀገር ወሊድ የቆንስላ ሪፖርት (CRBA) ቀጠሮ እንዴት ማስያዝ እችላለሁ?
በኢትዮጵያ የሚገኘው የዩኤስ ኤምባሲ አሁን የCRBA ማመልከቻዎችን በኤሌክትሮኒክስ (eCRBA) መቀበል ጀምሯል፡፡ እባክዎ ለዝርዝር መረጃ እና eCRBA በመጠቀም ማመልከት ይችሉ እንደሆነ ለማወቅ የሚከተለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ ፡- https://et.usembassy.gov/consular-report-of-birth-abroad-crba/
ማመልከቻውን እንደጨረሱ እና በ eCRBA ውስጥ አስፈላጊ ሰነዶችን ከጫኑ በኋላ የአሜሪካ ዜጋ አገልግሎት (ኤሲኤስ) ክፍልን ማመለከቻዎ ለቃለመጠይቅ ብቁ እንደሆነ የሚያሳውቁበት ሊንክ ያገኛሉ፡፡ የACS ክፍሉ ቀጠሮዎ መቼ እንደሆነ ያሳውቆታል፡፡ በኤምባሲው አገልግሎት የሚፈልግ እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ቀጠሮ ሊኖረው ይገባል። እባክዎን ማመልከቻዎ እንዳለቀ ለማሳወቅ ሲጽፉ ለከአንድ በላይ ልጅ የሚያመለክቱ ከሆነ ለብዙ ልጆች እንደሚያመለክቱ ለኤምባሲ ያሳውቁ እና በተመሳሳይ ቀን ለሁሉም አቅመ አዳም ላልደረሱ ልጆችዎ ፓስፖርት ወይም የCRBA አገልግሎቶች ቀጠሮ እንደሚፈልጉ ያሳውቁ AddisACS@state.gov ፡፡