ኢትዮጵያ ውስጥ ጋብቻ እየፈጸምኩ ነው። ትዳሬን በኤምባሲው ማስመዝገብ አለብኝ? ትዳሬ በአሜሪካ ውስጥ እውቅና ይሰጠዋል?

ጋብቻዎን ለአሜሪካ ኤምባሲ ወይም ቆንስላ ማሳወቅ አይጠበቅብዎትም።

በአጠቃላይ፣ በህጋዊ መንገድ የተፈፀሙ እና በውጭ ሀገር የሚሠሩ ጋብቻዎች በአሜሪካ ውስጥም እንዲሁ በህጋዊ መንገድ የሚሠሩ ናቸው። ሆኖም ግን፣ እያንዳንዱ የአሜሪካ ግዛት የራሱ የሆነ የጋብቻ ህግ አለው። ስለዚህ የጋብቻዎ እና የጋብቻ የምስክር ወረቀትዎ እዚያ የሚጸና መሆኑን ለማረጋገጥ የሚመለከተውን የግዛት ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማነጋገር አለብዎት።