ወደ አሜሪካ ወይም ኢትዮጵያ ምን መውሰድ ወይም በፖስታ መላክ እችላለሁ? ምን ዓይነት ምግብ/መድኃኒት/ ወዘተ. ማምጣት እችላለሁ?

የአሜሪካ ጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ (CBP) ድረ-ገጽ ወደ አሜሪካ መድኃኒት ወይም ምግብ ስለመውሰድ እና ስለታገዱ እና ስለተከለከሉ ዕቃዎች መረጃ ያቀርባል።

የአሜሪካ ጉምሩክ እና የድንበር ጥበቃ (CBP) ድረ-ገጽን በሚከተለው ላይ ይጎብኙ፦ https://www.cbp.gov/travel/us-citizens/know-before-you-go/prohibited-and-restricted-items

የአሜሪካ የፖስታ አገልግሎት (USPS) ድረ-ገጽ የተከለከሉ እና የታገዱ እቃዎች ዝርዝሮችን ጨምሮ ከአሜሪካ ወደ ውጭ አገር ስለመላክ መረጃ ያቀርባሉ።

የአሜሪካ የፖስታ አገልግሎት (USPS) ድረ-ገጽን ይጎብኙ፦ https://www.usps.com/ship/shipping-restrictions.htm ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የሚወስዱትን እቃዎች በተመለከተ መረጃ ለማግኘት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመለከተውን የመንግስት ባለሥልጣን መስሪያ ቤት ማነጋገር አለብዎት።